Meserete Kristos Choir/Mesgana Melkam New/Mesgana Melkam New

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ
ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ
ለጌታ ስግደትን ጨምሬ (፪x)

ሰናክሬም ጦር አሰልፎብኝ
የማደርገው ምንም ሲጠፋኝ
የምሥጋና መዝሙር ለጌታ
ስዘምር ጠላቶቼን መታ
አዝ
ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ
ለጌታ ስግደትን ጨምሬ

ሌሊቱን በሙሉ ስለፋ
አንድም የሚያዝ ዓሣ ጠፋ
ታንኳዬን ለጌታ ስሰጠው
መረቤን በዓሣዎች ሞላው
አዝ
ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ
ለጌታ ስግደትን ጨምሬ

ጳውሎስና ሲላስ በእስር ቤት
ተጥለው ሳሉ በእስራት
መዝሙር ሲዘምሩ ለጌታ
የእጃቸው ሰንሰለት ተፈታ
አዝ
ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ
ለጌታ ስግደትን ጨምሬ

ክፉ ሰልጥኖበት ሳዖል ላይ
አእምሮውን ስቶ ሲሰቃይ
ዳዊት በገና ሲደረድር
ክፉ መንፈስ ሸሸ ሲዘምር
አዝ
ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ለአምላኬ ዕልልታን ጨምሬ
ለጌታ ስግደትን ጨምሬ

ሁሉን ለሚችለው ለኢየሱስ
በእምነት አስረክቦ መፈወስ
በምሥጋና ሆኖ መቆየት
ባርኮት ይመጣል ከፀባኦት
አዝ
ምሥጋና ምሥጋና መልካም ነው ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ላምላኬ እልልታን ጨምሬ
ለጌታ ስግደትን ጨምሬ (፪x)