From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ።
|
አዝ፦ ምህረቱን ፡ ቸርነቱን
እዘምራለሁ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ልል ፡ እችላለሁ
እዘምራለሁ ፡ እጅግ ፡ ፈሶልኝ ፡ አይቻለሁ (፪x)
አብዝቼ ፡ ልወደው ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል
ብዙ ፡ የነበረው ፡ ኃጢአቴ ፡ ተፍቋል
ዝቅ ፡ ብዬ ፡ እግሮቹን ፡ በእምባዬ ፡ ላርሰው
ብልቃቱም ፡ ይሰበር ፡ ሽቶውን ፡ ላፍስሰው (፪x)
አዝ፦ ምህረቱን ፡ ቸርነቱን
እዘምራለሁ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ልል ፡ እችላለሁ
እዘምራለሁ ፡ እጅግ ፡ ፈሶልኝ ፡ አይቻለሁ
የኃጢአተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተባለ
ዘኪዮስ ፡ ሆይ ፡ ቤትህ ፡ ውላለው ፡ ስላለ
ዛሬ ፡ ቀን ፡ ለዚህ ፡ ቤት ፡ መዳን ፡ ሆኖለታል
ብሎ ፡ መድኃኒቴ ፡ ምህረትን ፡ አውጇል (፪x)
አዝ፦ ምህረቱን ፡ ቸርነቱን
እዘምራለሁ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ልል ፡ እችላለሁ
እዘምራለሁ ፡ እጅግ ፡ ፈሶልኝ ፡ አይቻለሁ
ምህረቱ ፡ ያዘኝ ፡ ከቤቱ ፡ እንዳልወጣ
ቸርነቱ ፡ በዛ ፡ አንዳች ፡ እንዳላጣ
በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ እያተከተሉኝ
አምላኬ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ በቤትህ ፡ አኖሩኝ (፪x)
አዝ፦ ምህረቱን ፡ ቸርነቱን
እዘምራለሁ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ልል ፡ እችላለሁ
እዘምራለሁ ፡ እጅግ ፡ ፈሶልኝ ፡ አይቻለሁ
|