Meserete Kristos Choir/Mesgana Melkam New/Endiet Talaq Neh

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ መሠረተ ክርስቶስ መዘምራን ርዕስ እንዴት ታላቅ ነህ አልበም ምሥጋና መልካም ነው

አዝ አቤት እንዴት ትላቅ ነህ እንዴት ታማኝ ነህ እንዴት ፍፁም ነህ የዘለዓለም አምላክ የማትለውጥ የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ (፪x)

በቃ አልፈልግም ልቤን ውሰደው አእምሮዬን ግዛው ለአንተ አድርገው ዝም ልበልና ኃይልህን ልመልከት ሌላው ሀሳቤ ይብቃ ይከተት አዝ አቤት እንዴት ትላቅ ነህ እንዴት ታማኝ ነህ እንዴት ፍፁም ነህ የዘለዓለም አምላክ የማትለውጥ የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ

ሌት በመኝታ እንዳስብ አንተን ቀን በሥራዬ እንዳጠነጥን መና ለነፍሴ እርካታና ደስታ ክብርህን ላስበው ሁሌ ጠዋት ማታ

አዝ አቤት እንዴት ትላቅ ነህ እንዴት ታማኝ ነህ እንዴት ፍፁም ነህ የዘለዓለም አምላክ የማትለውጥ የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ

እጄን በአፌ ላይ አድርጌ ተደነኩ ሥራህንም ሳየው በደስታ ተሞላሁ በእውነት ተረዳሁ የአንተን ታላቅነት እንዲሁም አስተዋልኩ የእኔን ታናሽነት

አዝ አቤት እንዴት ትላቅ ነህ እንዴት ታማኝ ነህ እንዴት ፍፁም ነህ የዘለዓለም አምላክ የማትለውጥ የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ

ለአንተ የሚገባህ ክብርህን ለመስጠት በመንፈስ ሳስብህ ያኔ ተረዳሁት አሁን ቃልኪዳኔ የመጨረሻው ተዋርጄ እንድኖር ነው ለአንተ የምሻው

አዝ አቤት እንዴት ትላቅ ነህ እንዴት ታማኝ ነህ እንዴት ፍፁም ነህ የዘለዓለም አምላክ የማትለውጥ የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ (፪x)