ዛሬም ፡ ያው ፡ ነው (Zariem Yaw New) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 4.jpg


(4)

ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘለዓለም
(Gieta Keber Lezelalem)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 3:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

በተዘጋ ቤት ውስጥ በፍርሃት ወድቀው

በሐዋርያት መሐል ድንገት ከተፍ ያለው

ሰላም ለእናንተ ይሁን አይዟችሁ ያላቸው

ሞቶ የተነሳው ጌታ ኢየሱስ ነው (2)

 

            ዛሬም ያው ነው

እኛን ከሃዘን ለማጽናናት

ጌታ አለው ልዩ ብርታት

 

    በባህር ሲጓዙ በጀልባ ተሳፍረው

      ያልታሰበ ማዕበል ድንገት አግኝቷቸው

      የተማመኑበት ሲጠፋ እምነታቸው

      ማዕበሉን ጸጥ በል ያለው ኢየሱስ ነው (2)

 

    ጌታን ከሐዋርያት ጋር ሊይዙት ባንድነት

       ተልከው ለመጡ ለቄሳር ሠራዊት

እነርሱን ልቀቁ እኔን ያዙኝ ያለው

ራሱን ለመስቀል ሞት የሰጠው የሱስ ነው (2)

 

    ገንዘቧን ጨርሳ ለባለ መድኃኒት

      በደም የተመታች ለአሥራ ሁለት ዓመት

      በፈውስ የጎበኛት ልብሱን ስትነካው

 

      ምስኪኗን ያነሳት ጌታ ኢየሱስ ነው (2)