የተጠማ ፡ ቢኖር (Yetetema Binor) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 4.jpg


(4)

ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘለዓለም
(Gieta Keber Lezelalem)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

የተጠማ ቢኖር እርካታ የራቀው

የህይወት ውሃን ምንጭ ጌታን ላስተዋውቀው

መጥገብን ለሚሻ እረሃብ ላጠቃው

የናዝሬቱ ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ነው

 

    ብዙ ለሮጠ ሰው እርካታ ፈልጎ

      ልቡን በማይረባ ነገር ላይ አድርጎ

      ለባዘነው ብዙ የምመክረው አለኝ

      ወደ የሱስ ይምጣ እረፍትን እንዲያገኝ

 

    ውሃ የማይዙ ጉድጓድን ቆፋሪ

      በቀዳዳ እንቅብ በረከት ሰፋሪ

      ሃብትም ቢሰበሰብ እርካታ ላጣ ሰው

      ለህይወቱ ትረጉም ጌታን ላስተዋውቀው

 

    ዓለምን ለማትረፍ ሕይወቱን ለጣለ

       ከውዱ ፈጣሪ ፊት ለኮበለለ

       ሮጦ ላላረፈ ነፍሱ ለምትባዝን

       ወደ አዳኙ ይምጣ ይታረቅ የሱስን

 

    እንደሚነዋወጥ ባህር ሰላም አጥቶ

      አዕምሮ መንፈሱ የሚያርፍበት ጠፍቶ

      ጭንቀቱ ለበዛ ሸክም ለከበደው

 

      ወደ ኢየሱስ ይምጣ አዳኝ ወደሆነው