ትጐበኛለህ ፡ አንተ (Tegobegnaleh Ante) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 4.jpg


(4)

ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘለዓለም
(Gieta Keber Lezelalem)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ትጎበኛለህ አንተም (2) ትጎበኛለህ

የማይለወጠው ጌታ ፍቅሩ ላንተም

እጅግ ልዩ ነው

 

    ቃል ኪዳን የገባልህ በእጆቹ መዳፍ ቀርጾህ

      ከቶውን አይረሳህም ለጠላት አይሰጥህም

      ታማኝነቱ ብዙ አይለወጥም እርሱ (2)

 

    ሃና ልጅ በማጣቷ ተገፋች በጣኡንቷ

      ለቅሶዋን ጌታ ሰምቶ ተመለከታት እራርቶ

      አንቺንም ሊጎበኝሽ ታማኝ ነው ጌታ አምላክሽ (2)

 

    ሰላሳ ስምንት ዓመት ተቆራኝቶት ሽባነት

      ተስፋውን ለቆረጠው የሱስ ነው የደረሰው

      ዛሬም ጌታ ለአንተም ፍቅሩ አይለወጥም (2)

 

    በአይን ያልታየውን በጆሮ ያልተሰማውን

      ያልታሰበ በሰው ልብ የሆነ ድንቅና ውብ

 

      ያን ነው ያዘጋጀልህ ጌታ ስለሚወድህ (2)