መተላለፌ ፡ ተደምስሶ (Metelalefie Tedemseso) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 4.jpg


(4)

ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘለዓለም
(Gieta Keber Lezelalem)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 2:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

መተላለፌ ተደምስሶ እንደ በረዶ ነፅቻለሁ ተመልከተኝ

      ሰይጣን እፈር በምን ትከሰኝ ይቅር ባይ አምላክ ይቅር ካለኝ

      ና ልጄ ብሎ እንደገና ታርቆኛልና ፈጣሪዬ ጠንክሬአለሁ

      አዲስ ሰው ሆኜ አገግሜአለሁ ጠላቴ ዋይ በል እኔ እስቃለሁ

      

    አሳች ነህና ልታስተኝ ብዙ ለፋህ ክስ አመጣህ በአዕምሮዬ

      ልትለየኝ ከፈጣሪዬ ምህረት ካገኘሁ ከጌታዬ

      መች እስከዛሬ የተጣለ የተረሳ ሰው አይተሃል በእርሱ ታምኖ

      የወደቀ ብኩን ሰው ሆኖ ምስክር አለሁ ማዳኑን ያየሁ

 

    ለዘለዓለም የኢየሱስ ደም በላዬ ላይ ወርዶ አጠበኝ ከኃጢአቴ

      ፈውስ አገኘሁ ከመድኃኒቴ በምን ትከሰኝ ዛሬስ ጠላቴ

      የመጣው ይምጣ ከእንግዲህስ በእርሱ እስካለሁሞት አልፈራም አመልከዋለሁ

      ይህን ስማ ቃል ኪዳን ነው የጌታ ስም ከሁሉ በላይ ነው