ለምኜው (Lemegniew) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 4.jpg


(4)

ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘለዓለም
(Gieta Keber Lezelalem)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ለምኜው ዘግቼ በሬን አደለኝ ሳለሁ ብቻዬን

ምስጢሬን አውቆታልና ለስሙ ይድረስ ምስጋና (2)

በልቤ ጓዳ ተዘግቶ ወቅትም ሲለወጥ አያረጅ

የነፍሴ ጩኸት ቢያውከኝ ሸክሜን አራገፍኩ በርሱ ደጅ (3)

በጋና ክረምት አለፉ እኔም እዛው ነኝ ደጃፉ

ቆይቼ ደጅ ጠናሁት ዘምበል ብሎም አየሁት

    ጉልበቴን አስገዛሁለት እጄን አነሳሁ ጓዳዬን

      የልቤን መሻት ለግሰኝ ታምራት አድርግ ብዬ

      በምስጢር እንደ ጠየኩት ሸሽጎ ሰጥቶኝ አየሁት

      ይመስገን ስሙን ባረኩት

 

    የእምነቴን ጎዶሎ ጽዋ በቸርነቱ አትረፍርፎ

      የሚንገዳገድ ተስፋዬን በብርቱ ክንዱ ደግፎ

      የምስኪን ጥሪ ተሰምቶት ዳሰሰኝ ከሰማይ መስኮት

      ፈቃዱን ማን ሰው ከልክሎት

 

    ጣሪያዬን ዘልቃ እንዳትሄድ ዲያቢሎስ ጸሎቴን ታግሎ

      ዝናቡን ውርጩን አዘዘ ሃሩር ንዳዱን አክሎ

      ጌታ ግን መብረቁን ጣለ ተገዳዳሪው የታለ

      መናዬ ዘንቦልኝ ዋለ

 

    የልብ አውቃ ምስጢረኛ የምስኪን ጽኑ ጓደኛ

     አንዲት ቀን ጠርቼው ነበር ላዋየው የግሌን ነገር

     ያሳቤን የውስጤን ምኞት ደጃፌን አየሁት ሞልቶት

 

     ፈቃዱን ማንስ ከልክሎት