አቤቱ ፡ ከአማልክት ፡ ሁሉ (Abietu Keamalekt Hulu) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 4.jpg


(4)

ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘለዓለም
(Gieta Keber Lezelalem)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ጊዜ ሳይለውጥህ ፀንተህ ትኖራለህ ለዘላለም

      ምድርና ሞላዋን በውስጧ ያለውን ነገር

      ብቻህን የፈጠርክ አምላክ ህያው ታላቅ እግዚአብሔር

 

    ሲሸበሸብለት ሲጮህለት ቢዋል

      መስማት ስለማይችል አልመለሰም በአል

      አንተ ግን ለኤልያስ ፈጥነህ መልሰሃል

      ክብርህን ለመግለጥ እሳት አውርደሃል

 

    ታላቁ አምላካቸው የፍልስጤማውያን

      ዳጎን ስላልቻለ ከአንተ ጋር ለመሆን

      በግንባሩ ወድቆ ለአንተ ሰገደልህ

      ሌላ አምላክ የለም አንተን የሚመስልህ

 

    ወልደ አዴር መጣ የሰው ምክር ሰምቶ

      ድል ሊያደርግ ፈልጎ ጦሩን አስከትቶ

      የተራራ ብቻ አምላክ መስለሃቸው

      በሜዳም ቢገጥሙህ ድል አደረግሃቸው

 

    ቸርነት ምህረት ፍቅር የተሞላህ

      እውነተኛ አምላክ ጌታ አንተ ብቻ ነህ

      ስለዚህም ልቤ በአንተ ላይ ጸና

 

      አንተን የሚመስል ሌላ የለምና