ለፍቅር ፡ ትርጉም (Lefeqer Tergum) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 1.jpg


(1)

እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው
(Endiet Denq Amlak New)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 2:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አዝ

አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕምም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ

1.ፍቅርን ፡ ሳስባት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስን ፡ አልማለሁ
መላ ፡ አካላቴን ፡ አየዋለሁ
ፍቅሩ ፡ ሆን ፡ በውስጥ ፡ እረዳለሁ
የፍቅር ፡ ትርጉም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም

2. ነፍስን ፡ ከመስጠት ፡ የበለጠ ፡ መውደድ ፡ የለም
ይህቺ ፡ ናትና ፡ ፍቅርም
ብርሃን ፡ የሆነች ፡ ለዚህ ፡ ዓለም
ፍቅርን ፡ ለማይት
ኢየሱስን ፡ መመልከት

አዝ፦ አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕምም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ (፪x)

3. በወልድ ፡ ልብ ፡ ውስጥ ፡ ያለች ፡ ፍቅር ፡ ነች ፡ ፍጹሚቱ
የገለጸልን ፡ በሞቱ
ያልተለወጠች ፡ በእርዛቱ
ፍቅርን ፡ ለመቅመስ
በኢየሱስ ፡ መታደስ

አዝ፦ አዝ፦ ፍቅሩ ፡ የማያቋርጥ ፡ ጅረት ፡ ነው
አጥንትን ፡ ዘልቆ ፡ የሚሰማ
ልዩ ፡ ጣዕምም ፡ የሞላው
የብርታት ፡ ቅኔ ፡ የሚያሰማ (፪x)