Meserete Kristos Choir/Endiet Denq Amlak New/Endiet Denq Amlak New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ መሠረተ ክርስቶስ መዘምራን ርዕስ እንዴት ድንቅ አምላክ ነው አልበም እንዴት ድንቅ አምላክ ነው

የደን ልማቱ የገደል ስርገቱ የወንዝ እርዝመቱ የቀላይ ውበቱ የቆንጆ ገጽታው የቦታው ከፍታው የባሕር ጥልቀቱ የሜዳ ስፋቱ እኛ የምናመልከው መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ የምናመልከው እንደምን ኃያል ነው እኛ የምንሰግድለት የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት (፪x)

የሽቶ መዓዛው የሙዚቃ ቃናው የለምለም እርካታው የመዝናኛ ቦታው የመፋቅር ወዙ የትዳር ማገዙ የፍጥረት ድምቀቱ የሰማይ ርቀቱ እኛ የምናመልከው መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ የምናመልከው እንደምን ኃያል ነው እኛ የምንሰግድለት የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት (፪x)

የአበቦች ፍካታ የወፎች ጫጫታ የቀለም መዋሃድ የሰው ልጅ መዋደድ የእምነት እርካታ ሰላምና ደስታ የፅዮን ውበቱ የእውነት ጥራቱ እኛ የምናመልከው መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ የምናመልከው እንደምን ኃያል ነው እኛ የምንሰግድለት የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት (፪x)

ጐህ ሲቀድ ማለዳ ጨለማ ሲከዳ የፀሐዩ ሙቀት የከዋክብት ብዛት የደመናት ክምር ንጹህ ተስማሚ አየር ሁሉን በስርዓት መሪ ለፍጥረቱ እኛ የምናመልከው መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ የምናመልከው እንደምን ኃያል ነው እኛ የምንሰግድለት የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት (፪x)