ዛሬም ፡ አላለቀም ፡ ትዕግሥቱ (Zariem Alaleqem Tigistu) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 8.jpg


(8)

ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
(Delu Yegietachen New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ዛሬም አላለቀም ትዕግሥቱ

ባንተ ላይ ምህረቱ

እየሱስ ሲጠራህ ተው ስማው ወደ ሞት አታዝግም

የፀጋ የምህረት ደጁ አልተዘጋም

 

    ቀንና ሌት ሳትል ስትለፋ ስትማስን

      ጥሪት ለመሰብሰብ ልትለውጥ ኑሮህን

      ለአምላክህ ጥሩ ጆሮ ዳባ ብለህ

      እረፍትና ሰላም ከየት ታገኛለህ ባክነህ ትቀራለህ

 

    ዓይንህ ሳይደነግዝ ወገብህም ሳይጎብጥ

       የራስህን ፈቃድ ለሌላ ሳትሰጥ

       እድሜ ሳይጫንህ ስትሮጥ እንደልብ

       በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ወደርሱ ተሰብሰብ

 

    በቀራንዮ መስቀል ፍርድ የተቀበለው

       ወንድሜ ከቅጣት ከሞት ሊያድንህ ነው

       ተው እልከኛ አትሁን ምክንያት አታብዛ

       ለክርስቶስ ፍቅር ራስህን አስገዛ አይለፍ እንደዋዛ

 

    ቀጠሮ ስትቀጥር ዘሬ ነገ ስትል

      ስለወደፊቱ የምታውቅ ይመስል

      በማታውቀው ሰዓት ሞት በድንገት መጥቶ

 

      ቀድሞ እንዳይወስድህ ከአምላክህ ለይቶ ሳታስበው ከቶ