የማያልፍ ፡ ሕይወት (Yemayalf Hiwot) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 8.jpg


(8)

ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
(Delu Yegietachen New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

የማያልፍ ህይወት በጌታዬ ተዘጋጅቷል መኖሪያዬ

       መከራ ጭንቅ ሃዘን በኑሮ ትካዜ

ከቶ የለም በዚያን ጊዜ በየሱስ ቤት በጌታዬ

ወዶኛልና መርጦኛልና ሊያከብረኝ ሊያነግሰኝ ጌታ ሞቷልና

ለዘላለም በምስጋና እኖራለሁ ከሱ ጋራ

 

    ጊዜው ሲደርስ የዚህ ዓለም ፍጻሜ

          ባይኔ አየዋለሁ ያዳነኝ ጌታዬን

          በእጅ ባልተሰራች ባምላኬ ከተማ

          ልኖር ቸኩያለሁ ከጌታዬ ጋራ

 

    የሰጠኝ ተስፋ ሲፈጸም ሲሞላ

         ሲመጣ አየዋለሁ በክብር ደመና

         በቅፅበት ዓይን እኔም ተለውጬ

         እቀበለዋለሁ ባየር ተነጥቄ

 

    ጌታ አልፏል ሲለኝ የቀደመው ስርዐት

          ኃዘንና ስቃይ ሞት የነበረበት

          እንባዎቼንም ሲያብስ ከአይኖቼ

          ናፍቀቴም ያበቃል ጌታዬን አይቼ

 

    ባዲሷ ጽዮን መካከሏ ካለው

          ከዙፋኑ ስር ፈልቆ ከሚፈሰው

          በህይወት ውሀ ከሚያፈራው ዛፍ ላይ

 

          ፍሬዋን እበላለሁ ሞትን ዳግም ሳላይ