ከመቃብር ፡ ወዲያ (Kemeqaber Wediya) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 8.jpg


(8)

ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
(Delu Yegietachen New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ዝናም ይከዳኛል ሃብትም ይተወኛል

  ቤቴም ይረሳኛል ሁሉም ይቅር

  የሱስ ያዋጣኛል (2)

 

    መልክ ረጋፊ ነው አሁን ያልፋል

      ቁመናም አንድ ቀን ይከዳኛል

      ሁሉም ይቅርና በጌታዬ ልፅና

      ዘላቂ ነውና ዘወትር ባለዝና

      ከመቃብር ወዲያ ሰጠኝ መጠለያ (2)

 

    ስመ ጥሩ አዋቂ ጠቢበኛ

      ወይም ደሃ ብሆን ችግረኛ

      ዝና የተረፈኝ ሆኜ በዚህ ብገኝ

      ከሞት ወዲህ ወዲያ ካላምላኬ ጉያ

      የላትም ማረፊያ ነፍሴ መጠለያ (2)

 

    ከሞት ወዲያ ማዶ ድል አድራጊ

      ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ታዳጊ

      ለኔ ሽልማቴ ጌጤ ውብ ንብረቴ

      በሞት ጥላ ስሄድ አንድም ነገር አልወስድ

 

      ሁሉን እተዋለሁ በየሱስ አርፋለሁ (2)