ክብር ፡ ይሁንለት (Keber Yehunelet) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 8.jpg


(8)

ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
(Delu Yegietachen New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አማኑኤል መጥቷል የፍቅር የሰላም

   የአንድነት መሰረት ክብር ይሁንለት

 

    አምላክ በሰው አድሮ በቅድስተ ድንግል

       ከክብሩ ተዋርዶ ሊያነጻን ከበደል

       የአንድነት መሰረት መድኃኒተዓለም

       ተወልዷል ከፍ ይበል እናውጅ ለዓለም (2)

 

    የዳዊት ከተማ ቤተልሄሚቱ

       በአንቺ የተወለደው ንጉሠ ነገሥቱ

       ዛሬም በምድር ዙሪያ ይሰማል አዋጁ

       በኃጢአት የተዘጋው እንዲከፈት ደጁ (2)

 

    የሃጢአት ቀንበር ጫንቃችን ተጭኖት

       ተስፋችን ጨልሞ ከቦን የሞት ፍርሃት

       ጽድቅን አልባሻችን የደካሞች ጉልበት

       የሱስ ተወለደ ክብር ይሁንለት (2)

 

    በዝሙት በስካር በነፍስ ገዳይነት

      በህመም በደዌ ታስራችሁ በሃጢአት

      የተቸገራችሁ ጠፍቷችሁ መንገዱ

 

     ወደ እየሱስ ኑና ዳግም ተወለዱ (2)