ጌታ ፡ እውነተኛ ፡ ነው (Gieta Ewnetegna New) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 8.jpg


(8)

ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
(Delu Yegietachen New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ጌታ እውነተኛ ነው አይዋሽም

      የሰጠውን ኪዳን አይረሳም

      ይልቅ ታገስና ጠብቀው ጥቂት ነው የቀረው

 

 

     ኦ ወንድም ራዕዩ ቸኩሏል ወደ ፍፃሜውም ገስግሷል

     ኦ እህት ራዕዩ ቸኩሏል ተሰፋው እውን ሊሆን ጊዜው ቀርቧል

     ይህ የድንኳን ኑሮ አሁን ያበቃል (2)

 

    አይታይህም ወይ ዘመኑ

የኖህ ጊዜ ፀባይ መግነኑ

ታዲያ ምነው ልብህ ራደ ስለምን ከበደ

 

    ጌታ እየሱስ ከላይ በስልጣን

ከመላዕክቱ ጋራ ይመጣል

ያኔ ብድራትህን ታያለህ ትፈነድቃለህ

 

    አሜን ጌታችን ሆይ ቶሎ ና

የቅዱሳንህ ልብ ናፍቋልና

 

አንተ የንጋት ኮከብ ብቅ በል እኛም እፎይ እንበል