From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው ፡ ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው ፡ ድሉ
ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
ጠላትን ፡ ረገጠ ፡ አርነት ፡ አወጀ
ለኛ ፡ ለልጆቹ ፡ ማረፊያ ፡ አዘጋጀ
ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው
ከዲያቢሎስ ፡ ወጥመድ ፡ ልንድን
በጌታችን ፡ ብርታት ፡ ተሞላን
እንግዲህ ፡ እንገስግስ ፡ አንተኛ
የኢየሱስ ፡ ነን ፡ እኛ
አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው ፡ ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው ፡ ድሉ
ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
ጠላትን ፡ ረገጠ ፡ አርነት ፡ አወጀ
ለኛ ፡ ለልጆቹ ፡ ማረፊያ ፡ አዘጋጀ
ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው
እስራኤልን ፡ ከግብፅ ፡ ያወጣ
ፈርኦንን ፡ በባህር ፡ የቀጣ
ይህን ፡ ታዳጊ ፡ አምላክ ፡ አምነናል
በድል ፡ ይመራናል
አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው ፡ ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው ፡ ድሉ
ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
ጠላትን ፡ ረገጠ ፡ አርነት ፡ አወጀ
ለኛ ፡ ለልጆቹ ፡ ማረፊያ ፡ አዘጋጀ
ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው
ኢያሱ ፡ ጌዲዮንና ፡ ዳዊት
አብርሃምና ፡ ሙሴ ፡ ያለፉት
የእምነትና ፡ የጦር ፡ አርበኞች
የድል ፡ ምሳሌዎች
አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው ፡ ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው ፡ ድሉ
ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
ጠላትን ፡ ረገጠ ፡ አርነት ፡ አወጀ
ለኛ ፡ ለልጆቹ ፡ ማረፊያ ፡ አዘጋጀ
ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው
የጠላት ፡ ማሽካካት ፡ ድንፋታ
የሰልፍ ፡ የጦር ፡ ብዛት ፡ ጋጋታ
ለሃያሉ ፡ ኢየሱስ ፡ ምኑ ፡ ነው
ሁሉም ፡ በእጁ ፡ ነው
አዝ፦ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው ፡ ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው ፡ ድሉ
ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
ጠላትን ፡ ረገጠ ፡ አርነት ፡ አወጀ
ለኛ ፡ ለልጆቹ ፡ ማረፊያ ፡ አዘጋጀ
ድሉ ፡ ያምላካችን ፡ ነው
|