ዳዊት ፡ ለእግዚአብሔር (Dawit Legziabhier) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 8.jpg


(8)

ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
(Delu Yegietachen New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ከሚልኮልም አፍ ቢወርድም ስድቡ

ቆነጃጅቱ በንቀት ቢያዩ

እርሱ ግን ካምላክ ነበር ጉዳዩ (2)

 

ሞትን በህይወት ለለወጠልን የማይሰፈር ውለታ አለብን

በምስጋና ድምጽ እንግባ ሰማይ ወደ ታደገን እንይ ወደ ላይ

 

    ክብር ለእርሱ ይዋረድ የቆመው ለእርሱ ይስገድ

      እግርም ያለመጫሚያ መጎናጸፊያም ይውለቅ

      ይሉኝታን ጉያው አቅፎ ዛሬም የሚያባብላት

      ከሰማዩ በረከት አያገኝም በሙላት

 

    እስትንፋሱ በአፍንጫው ያለበት ታናሹ ሰው

      ሁሉን ከሚችል ጋራ ቢመዘን ገለባ ነው

      ምስጋና ለሚገባው ሞገሱ ለሚያስፈራው

      ነገሥታቱም ይስገዱ ታቦቱም ፊት ጭፈራው

 

    እልልታው እስከ ማዶ ጭብጨባው በመንደሩ

      መቅደሱን ሞልቶ ይፍሰስ ያስተጋባ መዝሙሩ

      ያከበረን ይናቀን የሳቀልን ያኩርፈን

 

      እኛ ግን እንደ ዳዊት ከጌታ ጉዳይ አለን