ብቻውን ፡ አምላክ (Bechawen Amlak) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 8.jpg


(8)

ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው
(Delu Yegietachen New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ብቻውን አምላክ ብቻውን ጌታ (2)

እግዚአብሔር ኃያል አልፋ ኦሜጋ

 

    ሰማይና ምድርን ሲሰራው አስውቦ (2)

      ያገዘውስ ማነው ሰው ሲፈጥር ደግሞ

      ሁሉንም ሠርቶታል ግሩም ድንቅ አድርጎ

      ለኤልሻዳይ ጌታ ለብቻው አምልኮ (2)

 

    እርሱ ብቻ ጌታ ብቻውን አምላክ ነው (2)

      ያለና የሚኖር ሁሉን የሠራ ነው

      ከማን ጋር ነው ኃይሉን ምናመሳስለው

      የአማልክቶች አምላክ የጌቶች ጌታ ነው (2)

 

    ብቻውን ሊመለክ ሊከብር ይገባዋል (2)

      ማን እኩያ አለው ማንስ ይመስለዋል

      ሰማይና ምድርን በክብሩ ሞልቶታል

      ሁሉን ከስልጣኑ በታች አድርጎታል (2)

 

    ኃያል ነህ ገናና ነግሠሃል ብቻህን (2)

      በብዙ ምስጋና እናመልክሃለን

      አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ጌታችን አንድ አምላክ

 

      ካንተ በቀር እኛ ሌላ አምላክም አናውቅም (2)