የአማልክት ፡ አምላክ (Yeamalekt Amlak) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 3.jpg


(3)

አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
(Ante Talaq Neh)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

የአማልክት አምላክ የነገሥታት ንጉሥ

       በዙፋኑ ያለ ስሙ የእስራኤል ቅዱስ

ፍጥረታትን ሁሉ እርሱ ያስተዳድራል

ኤልሻዳይ እግዚአብሔር ክብር ይገባሃል

 

    ፍልስጤም ወሰደ የእግዚአብሔርን ታቦት

       በቤቱ አኖረው በጣዖት ፊት ለፊት

       መቆም ከቶ አልቻለም ዳጎን ተሰበረ

       በባእዳን ምድር እግዚአብሄር ከበረ

 

    ቢታበይ በእግዚአብሄር ናቡከደነፆር

      ከዙፋኑ አውርዶ ሰደደው ወደ ዱር

      ለሚሾም ለሚሽር ለኖረ በስልጣን

      ለነገስታት ንጉስ ለእግዞአብአሄር ክብር ይሁን

 

    ኪሩቤል በፊቱ ወድቀው ይሰግዳሉ

ቅዱስ (3) እግዚአብሔር እያሉ

      በአርያም መቅደሱ በክብር ልዕልና

      በዙፋኑ ላለ ለእግዚአብሔር ምስጋና

 

    ሰማይ ዙፋኑ ነው ምድር መረገጫው

      ደመና የእግሩ ትቢያ ግርማው አስፈሪ ነው

      ውሆችን በእፍኙ ሰማይን በስንዝር

 

      ሊለካ ለሚችል ክብር ለእግዚአብሔር