ምስኪን ፡ ወደአንተ ፡ ሲጠጋ (Meskin Wedante Sitega) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 3.jpg


(3)

አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
(Ante Talaq Neh)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 3:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ትዕቢት ፡ የተሞላው ፡ ጐልያድ ፡ ወደቀ
በአንተ ፡ የታመነውን ፡ ዳዊትን ፡ የናቀ
አንተን ፡ ይዞ ፡ ወጥቶ ፡ ታናሽ ፡ ብላቴና
ግዙፉን ፡ ዘረረው ፡ ስምህን ፡ ጠራና

አዝ፦ ምስክኪን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ሲጠጋ ፡ ጋሻ ፡ መከታ ፡ ፍለጋ
ገፍተኸው ፡ መቼ ፡ ታውቃለህ ፡ በእቅፍህ ፡ ታኖረዋለህ
በቅዱስ ፡ ድንኳንህ ፡ ያድራል ፡ በቤትህ ፡ የለመልማል
ሰላሙን ፡ ታበዛዋለህ ፡ ጠላቱን ፡ ትመታዋለህ
ጠላቱን ፡ ትመታዋለህ!

የሚጤሰውን ፡ ጧፍ ፡ ከቶ ፡ አታጠፋም
የተቀጠቀጠ ፡ ሸምበቆ ፡ አትሰብርም
ድካሙን ፡ ተረድቶ ፡ አንተን ፡ የተጠጋ
በቅዱሱ ፡ ስፍራ ፡ ከበረ ፡ ከአንተ ፡ ጋር

አዝ፦ ምስክኪን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ሲጠጋ ፡ ጋሻ ፡ መከታ ፡ ፍለጋ
ገፍተኸው ፡ መቼ ፡ ታውቃለህ ፡ በእቅፍህ ፡ ታኖረዋለህ
በቅዱስ ፡ ድንኳንህ ፡ ያድራል ፡ በቤትህ ፡ የለመልማል
ሰላሙን ፡ ታበዛዋለህ ፡ ጠላቱን ፡ ትመታዋለህ
ጠላቱን ፡ ትመታዋለህ!

መሰማሪያ ፡ አጥቶ ፡ የባዘነ ፡ ሕይወት
መቅበዝበዙ ፡ ቀረ ፡ ሲገባ ፡ በአንተ ፡ ቤት
እንደለመለመ ፡ የወይራ ፡ ዛፍ ፡ ሆኗል
ምስኪኑ ፡ በአንተ ፡ ይኸው ፡ ከፍ ፡ ብሏል

አዝ፦ ምስክኪን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ሲጠጋ ፡ ጋሻ ፡ መከታ ፡ ፍለጋ
ገፍተኸው ፡ መቼ ፡ ታውቃለህ ፡ በእቅፍህ ፡ ታኖረዋለህ
በቅዱስ ፡ ድንኳንህ ፡ ያድራል ፡ በቤትህ ፡ የለመልማል
ሰላሙን ፡ ታበዛዋለህ ፡ ጠላቱን ፡ ትመታዋለህ
ጠላቱን ፡ ትመታዋለህ!

ስምህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ የጸና ፡ ግንብ ፡ ነው
ለደካማው ፡ ብርታት ፡ ለምስኪን ፡ መጠጊያው
ያስጨናቂን ፡ ቀንበር ፡ ጸባብራለህ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ በቅን ፡ ትፈርዳለህ

አዝ፦ ምስክኪን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ሲጠጋ ፡ ጋሻ ፡ መከታ ፡ ፍለጋ
ገፍተኸው ፡ መቼ ፡ ታውቃለህ ፡ በእቅፍህ ፡ ታኖረዋለህ
በቅዱስ ፡ ድንኳንህ ፡ ያድራል ፡ በቤትህ ፡ የለመልማል
ሰላሙን ፡ ታበዛዋለህ ፡ ጠላቱን ፡ ትመታዋለህ
ጠላቱን ፡ ትመታዋለህ!