ምንድንነው ፡ ያጓጓህ ፡ በዓለም (Mendenew Yaguaguah Bealem) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 3.jpg


(3)

አልበም
(3)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ምንድነው ያጓጓህ በዓለም
ተው እንደ ሰማዩ የለም
በምድር ታላቅ ብትሆን ለጊዜው ነው
የሰማዩ መንግሥት ዘላለም ነው
    ዝና ይሰጥሃል የምድር ላይ ሹመትህ
    ግን የቱ ይበልጣል እስቲ ልጠይቅህ
    የሰማዩ መንግሥት ወኪል ከመሆንህ (2)

    ፀጋ የሌለበት ክብር ከመቀበል
    አሟሟቱ ሳያምር እንዲያው ከመጎስቆል
    መኖር ይመረጣል መስቀሉ ሥር መጣል (2)

    ለሁለት ጌታዎች መገዛት አትችልም
    ምርጫህን አስተካክል ከየሱስ ከዓለም
    ማንን ትመርጣለህ ጌታህ ማነው ወንድም (2)

    ሃብት ብልጥግና ሁሉም ይጠፋሉ
    ሰማያት እንደልብስ ይጠቀለላሉ
    ጌታ በደጅ ነው ተዘጋጅ ይላሉ (2)