ሊመጣ ፡ ነው ፡ ሙሽራው (Limeta New Musheraw) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 3.jpg


(3)

አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
(Ante Talaq Neh)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 3:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ሊመጣ ነው ሙሽራው

ሊገለጥ ነው ኢየሱስ 2

 

    ነፍሴ በናፍቆት ምትጠብቀው የይሁዳ አንበሳ ድል አድራጊው

       በግርማ በክብር ሊገለፅ ነው

      አሜን ሙሽራው ሊመጣ ነው (2)

 

    ፍጥረት እሩጫ ሊያበቃ ነው ግዛቱም ለየሱስ ሊሆን ነው

      የሰላም ንጉሥ ሊገለጥ ነው

      አሜን ኢየሱስ ሊመጣ ነው (2)

 

    በአዲስ ሰማይ በአዲስ ምድር ልንኖር አብረን ከጌታ ጋር

      ያ ታላቁ ሠርግ ደረሰልን

      አሜን ሙሽራው ሊመጣልን ነው (2)

 

    አለቀ እንግዲህ ዘመን መጣ እየሱስ በክብር ሊመጣ

እንባዬን ከአይኔ ሊያብስልኝ

አሜን ላርፍ ነው ጥቂት ቀረኝ (2)

 

    አሳቹ ስራው ሊገለጥ ነው የእግዚኣብሔር ጠላት ሊወድቅ ነው

      ዲያቢሎስ ወደ እሳት ሊጣል ነው

 

      አሜን ንጉሱ ሊገለጥ ነው (2)