ብዙ ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩ (Bezu Bezu Feqru) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 3.jpg


(3)

አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
(Ante Talaq Neh)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 3:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ብዙ ብዙ ፍቅሩ ብዙ ብዙ ምህረቱ

ብዙ ብዙ ቸርነቱ አቆመን በቤቱ

 

    ጌታ ብዬ የምጠራው አዲስ ቅኔ የምቀኘው

       እግሬም ፀንቶ የቆመው

       በእኔ አይደለም በእርሱ ነው

       ምህረቱ ብዙ ነው

 

    መድኃኒቴን ሳስከፋ ገበታውን ስደፋ

      ማረኝ ብዬ ግን ሳለቅስ

      በእጆቹ በመዳሰስ

      እንባዬን በማበስ

 

    በብርቱ ሰልፍ ያቆመኝ በውጊያ ድል የሰጠኝ

       ኃጢአት ስትከበኝ በድካሜ እያገዘኝ

       ፍቅሩን እያሰየኝ

 

    በጠላቴ ፊት ለፊት ራሴን ሲቀባ ዘይት

       ሲያስተናግደኝ ተግቶ

       ገበታን አዘጋጅቶ ቸርነቱ በዝቶ

 

    እግዚአብሔር አባቴ ይክበር ይንገሥ በሕይወቴ

      ይህንን አይቻለሁ ጌትነቱ የፍቅር ነው

 

      ፍጥረት ሁሉ ያንግሠው