አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (Ante Talaq Neh) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 3.jpg


(3)

አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
(Ante Talaq Neh)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አንተ ታላቅ ነህ እኩያ የሌለህ

አንተ ቅዱስ ነህ ነውር የሌለብህ

አንተ (2) ለዘላለም ያው አንተ ነህ

 

    በሰማይ በምድር የከበርክ

      ፍጥረትን ለብቻህ የፈጠርክ

      የኔን ልብ ማደሪያ ያረከው

      አምላኬ (3)

 

    አዕላፍ መላዕክት የሚሰግዱልህ

      ቅዱሳን የሚዘምሩልህ

      ፍቅር ግን ከእኔ ጋር ያረገህ

      ጌታዬ(3)

 

    በሰው ዘንድ ተንቀህ ያለፍከው

      እድፈቴን በደምህ ያጠብከው

      ቅጣቴን የተቀበልክልኝ

      አዳኜ (3)

 

    በግርማ የምትገለጸው

      በሁሉም በቅን የምትፈርደው

 የናቁህ የወጉህ የሚያዩህ

 

      እየሱስ (3)