ተመስገን ፡ እስከዚህ ፡ ሰዓት (Temesgen Eskezih Seat) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ድቅድቅ ጨለማውን ዘመን አልፈን ዛሬ ብርሃን አየን
ተመስገን ጌታ እግዚአብሔር በምድር በሰማይ ተከበር
አዝ፦ ተመስገን እስከዚህ ሰዓት ያደረስከን
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እኛ ማን ነን
መስዋዕት እንሰዋ ተንበርክከን ተመስገን (3)
ከመከራው ሸክም ብዛት ጎብጠን ባለፉት ዓመታት
ቀና ብለን እንድንራመድ ላበቃን ጌታ እንስገድ
አዝ፦ ተመስገን እስከዚህ ሰዓት ያደረስከን
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እኛ ማን ነን
መስዋዕት እንሰዋ ተንበርክከን ተመስገን (3)
ሐብታችንን ተቀምተን ከቤት ከሃገራችን ወጥተን
ስቅስቅ ብለን አልቅሰናል ይህን አይተህ እረድተኸናል
አዝ፦ ተመስገን እስከዚህ ሰዓት ያደረስከን
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እኛ ማን ነን
መስዋዕት እንሰዋ ተንበርክከን ተመስገን (3)
ሰዎች ተዘባበቱብን የዓለም ጉድፍ አደረጉን
ዛሬ ይኸው እንደገና አቁሞናል ለምስጋና
አዝ፦ ተመስገን እስከዚህ ሰዓት ያደረስከን
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እኛ ማን ነን
መስዋዕት እንሰዋ ተንበርክከን ተመስገን (3)
በደመና እስክትመለስ የዓለም ስደት ልንታገስ
ለዚህ ተጠርተናልና ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና
አዝ፦ ተመስገን እስከዚህ ሰዓት ያደረስከን
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እኛ ማን ነን
መስዋዕት እንሰዋ ተንበርክከን ተመስገን (3)
|