ነፍስህ ፡ ካለችበት (Nefseh Kalechebet) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 2.jpg


(2)

አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
(Amien Belu Segedulet)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 3:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አዝ፦ ነፍስ ካለችበት ከጥልቁ ሸለቆ
ያወጣታል አውቆ ኢየሱስ መንጥቆ

ባርኮት የሞላበት የፊቱ ህይወትህ
ባላሰብከው ሰዓት በቅጽበት ጠፍቶብህ
የምታለቅስ ሰው ሆይ አይዞህ ክንድህ ይጽና
የማታ የማታ ድል ያንተ ነውና (2)

አዝ፦ ነፍስ ካለችበት ከጥልቁ ሸለቆ
ያወጣታል አውቆ ኢየሱስ መንጥቆ

አምላክ ከፋ አትበል አታጉረምርም ፈጥነህ
ቢቆይም ዋጋ አለው የጸሎት ላይ እንባህ
አሁን ከጽዮን ውጭ እንዳለህ ቢመስልህ
ያምላክ ድምፅ ሲሰማህ ነገ ሌላ ሰው ነህ (2)

አዝ፦ ነፍስ ካለችበት ከጥልቁ ሸለቆ
ያወጣታል አውቆ ኢየሱስ መንጥቆ

የምሬት ጩኸትህ ለቅሶህን ሁሉ አይቶ
ይክስሃል ጌታ በበረከት ሞልቶ
ገሸሽ የሚል አምላክ እንደሌለህ አምነህ
ጉልበትህን በግድ አስገዛ ለአምላክህ (2)

አዝ፦ ነፍስ ካለችበት ከጥልቁ ሸለቆ
ያወጣታል አውቆ ኢየሱስ መንጥቆ