ነዶ ፡ ነዶ ፡ እሳቱ (Nedo Nedo Esatu) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 2.jpg


(2)

አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
(Amien Belu Segedulet)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አዝ፦ ነዶ ነዶ እሳቱ የመንፈስ ቅዱስ ዘይት ሙላቱ
የጌታን ብርሃን እያበራ
አየሁት ዛሬም እንደገና ምስጋና
የኢየሱስ ሥራ ድንቅ ነውና ምስጋና
ለሆነው ገናና

ላዘነው መጽናናት ሰጥቶ ለደከመው ጉልበት ሞልቶ
ኃያል አምላክ ብርቱ ተዋጊ በብርታቱ ድል አድራጊ
በክንፎቹ ላባ ከልሎን ከበረሃው ሃሩር ጋርዶን አለምልሞ ዳግም አቆመን
እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን

አዝ፦ ነዶ ነዶ እሳቱ የመንፈስ ቅዱስ ዘይት ሙላቱ
የጌታን ብርሃን እያበራ
አየሁት ዛሬም እንደገና ምስጋና
የኢየሱስ ሥራ ድንቅ ነውና ምስጋና
ለሆነው ገናና

ፍርሃት ወድቆበት ጉብዝና እንኳን ሌላውን ለያጽናና
የሚነድ እሳት ተዳፍኖበት ተስፋ መቁረጥ ተጭኖበት
ድንገት ቦግ አለ መብራቱ ተቀጣጠለም እሳቱ
ማን ሊያጠፋው ሰደድ ነዶ መንፈስ ቅዱስ እሳት ወርዶ

አዝ፦ ነዶ ነዶ እሳቱ የመንፈስ ቅዱስ ዘይት ሙላቱ
የጌታን ብርሃን እያበራ
አየሁት ዛሬም እንደገና ምስጋና
የኢየሱስ ሥራ ድንቅ ነውና ምስጋና
ለሆነው ገናና

ነፍሴን ሊያጠፋ ከተነሳው ወጥመድን ከፊቴ ካስቀመጠው
ከክፉ ኃይል ካሴረብኝ ጌታ ቀድሞ ተዋጋልኝ
ሰይፉን መዞ ጦሩንም ሰብቆ ከሚያስፈራራኝ ነፍሴን አንቆ
በቀን በሌት ቅጥሬን ጠበቅህ ጌታ ክበር በዙፋንህ

አዝ፦ ነዶ ነዶ እሳቱ የመንፈስ ቅዱስ ዘይት ሙላቱ
የጌታን ብርሃን እያበራ
አየሁት ዛሬም እንደገና ምስጋና
የኢየሱስ ሥራ ድንቅ ነውና ምስጋና
ለሆነው ገናና

የወንጌሉን ቃል እየዘራ በኃይል በሥልጣን እየሠራ
በሩቅ ሃገር በኃጢአት ያሉ የጌታን ማዳን ተቀበሉ
በሽተኞችም ተፈወሱ በምህረት እጆች ተዳሰሱ
በአጋንንት ኃይል የታሰሩ ቀንበሮቻቸው ተሰበሩ

አዝ፦ ነዶ ነዶ እሳቱ የመንፈስ ቅዱስ ዘይት ሙላቱ
የጌታን ብርሃን እያበራ
አየሁት ዛሬም እንደገና ምስጋና
የኢየሱስ ሥራ ድንቅ ነውና ምስጋና
ለሆነው ገናና