ምሥጋና ፡ ምሥጋና (Mesgana Mesgana) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 2.jpg


(2)

አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
(Amien Belu Segedulet)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ
በዕልልታ ፡ በዕልልታ ፡ በሽብሸባ ፡ በሽብሸባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ

እጅግ (፫x) ፡ የከበረ
ሥሙም ፡ ያለ ፡ የሚኖር ፡ የነበረ
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነውና
ልግባ ፡ ላምላኬ ፡ ልሰጥ ፡ ምሥጋና

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ
በዕልልታ ፡ በዕልልታ ፡ በሽብሸባ ፡ በሽብሸባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ

ምርኮኛ ፡ የነበርኩ ፡ ለጠላት
ባለ ፡ እግርና ፡ ባለ ፡ እጅ ፡ ሰንሰለት
ዛሬ ፡ ግን ፡ የታል ፡ ተበጣጥሷል
የሞት ፡ ድምጽ ፡ ከእኔ ፡ ተወግዷል

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ
በዕልልታ ፡ በዕልልታ ፡ በሽብሸባ ፡ በሽብሸባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ

እጅግ ፡ ወደ ፡ አማረ ፡ ማደሪያው
ብዙ ፡ በረከት ፡ ወደ ፡ ሚያፈሰው
እንድገባ ፡ ወዶኛልና
ልስገድ ፡ ልቀኝ ፡ በደስታ ፡ ዜማ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ
በዕልልታ ፡ በዕልልታ ፡ በሽብሸባ ፡ በሽብሸባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ

ውርደቴን ፡ በክብር ፡ ለውጧል
ሸክሜን ፡ ከላዬ ፡ ላይ ፡ አንስቷል
ለምን ፡ እሆናለሁ ፡ እንዳልተፈታ
እስኪ ፡ ላዚምለት ፡ በእልልታ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ
በዕልልታ ፡ በዕልልታ ፡ በሽብሸባ ፡ በሽብሸባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ