ምንም ፡ ነገር ፡ የለንም (Menem Neger Yelenem) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ምንም ነገር የለንም የኛ ነው የምንለው
ከአምላክ ያልተሰጠን ከላይ ያላገኘነው
ሁሉም የጌታችን ነው የቱን እኛ አተረፍን
ክብርና ሞገሳችን የሱስ ነው ፀጋን ያለበሰን
አዝ፦ አሜን በሉ ስለስጦታው አመስግኑት ስለውለታው
ሁለንተናችን የሱስ አብዝቶ ሰጠን ሁሉን (2)
የኛ እጃችን ባዶ ነው ጌታ ግን ይሞላናል
የኛ ለኛ የሆነው መኖሪያችን ምንድነው
ሁሉን በሱ አገኘን ባዶ ሸክላዎች ሳለን
ክብርና ሞገሳችን የሱስ ነው ፀጋን ያለበሰን
አዝ፦ አሜን በሉ ስለስጦታው አመስግኑት ስለውለታው
ሁለንተናችን የሱስ አብዝቶ ሰጠን ሁሉን (2)
የቱ ነው የእኛ ሃብት ውሃ አየር ፀሐይ ናት
ወይ እንቁ ወርቅ ከምድር ሊያሰመካን የሚደፍር
ይህ አለኝ የምንለው ለዚህ ዓለም የሰጠነው
ሁሉን በጌታ የሱስ አገኘን ፀጋን ባለበሰን
አዝ፦ አሜን በሉ ስለስጦታው አመስግኑት ስለውለታው
ሁለንተናችን የሱስ አብዝቶ ሰጠን ሁሉን (2)
ክብር ሃሌሉያ በሉ ጌታ ሰጥቶናል ሁሉን
እርሱን የሚያህል ምስጋና ይገባዋልና
ምንም ነገር ሳይኖረን ክቡር ሰው ያደረገን
ይክበር ይመስገን የሱስ ጌታችን ፀጋን ያለበሰን
|