ከአቅም ፡ በላይ ፡ የለብኝ ፡ ፈተና (Keaqem Belay Yelebegn Fetena) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 2.jpg


(2)

አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
(Amien Belu Segedulet)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 3:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

በአንበሳ ጉድጓድ ተጥዬ እያየሁኝ
ጥርሳቸው አልነክስም ብሎ እኔ ዳንኩኝ
በእሳት ነበልባል ማለፍ ይቻለኛል
በዚያው መጠን ፀጋው ልባስ ይሆነኛል

አዝ፦ ምስጋና (3)
ከአቅሜ በላይ የለብኝ ፈተና
ለእንዲህ ላለ መቅሰፍት አይተወኝምና
ለእግዚአብሔር ምስጋና

ከፈተናው ደጃፍ ገና ከመቅረቤ
ተንቧ ተንቧ ይላል ወየው ይላል ልቤ
ግን መግባት ስጀምር እግሮቼን ሳነሳ
ግዙፉ ፈታኜ ይሆናል ኮሳሳ

አዝ፦ ምስጋና (3)
ከአቅሜ በላይ የለብኝ ፈተና
ለእንዲህ ላለ መቅሰፍት አይተወኝምና
ለእግዚአብሔር ምስጋና

ዙሪያዬ ፀጥ ቢል አንዳችም ሰው ባይደርስ
የኔን ክፉ አይወድም ይገኛል ኢየሱስ
የውዴ ፍቅር ቃል ተራሮች ይዘላል
በኮረብታዎች ላይ ተወርውሮ ይመጣል

አዝ፦ ምስጋና (3)
ከአቅሜ በላይ የለብኝ ፈተና
ለእንዲህ ላለ መቅሰፍት አይተወኝምና
ለእግዚአብሔር ምስጋና