ከአንተ ፡ ወደማን (Keante Wedeman) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 2.jpg


(2)

አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
(Amien Belu Segedulet)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አዝ፦ ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን (2)
አንተ የዘላለም የህይወት ቃል አለህ
አንተን የሕይወት ውሃ ምንጭ ትተን
ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን

ሁሉን ነገር ትተን አንተን ተከተልን
መረባችን ጣልን በፍቅርህ ተማርከን
ካለም ዕድል ፈንታ ድርሻ ስለሌለን
ካንተ ካምላካችን ወዴት እንሄዳለን (2)

አዝ፦ ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን (2)
አንተ የዘላለም የህይወት ቃል አለህ
አንተን የሕይወት ውሃ ምንጭ ትተን
ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን

ወጀብ ማዕበሉ እጅግ ሲያስጨንቀን
ካንተ ሌላ ማነው ፈጥኖ የደረሰልን
በቤትህ ውስጥ ስኖር ምንም አልጎደለን
ካንተ ካምላካችን ወዴት እንሄዳለን (2)

አዝ፦ ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን (2)
አንተ የዘላለም የህይወት ቃል አለህ
አንተን የሕይወት ውሃ ምንጭ ትተን
ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን

የአሁን ዘመን ዴማስ መሆን አንፈልግም
ካንተ ከአምላካችን ዓለምን አንመርጥም
ብድራታችንን ትኩር ብለን አይተን
እስከ መጨረሻው በአንተ እንፀናለን (2)

አዝ፦ ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን (2)
አንተ የዘላለም የህይወት ቃል አለህ
አንተን የሕይወት ውሃ ምንጭ ትተን
ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን

የዚህ ዓለም መከራ ምንም ሳይበግረን
ጠላት ዲያቢሎሰን በስምህ ተቃውመን
በአንተ መሪነት ጽዮን እንደርሳለን
ሞትም ቢሆን ሕይወት ከአንተ ሳይለየን (2)

አዝ፦ ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን (2)
አንተ የዘላለም የህይወት ቃል አለህ
አንተን የሕይወት ውሃ ምንጭ ትተን
ካንተ ወደ ማን እንሄዳለን