እረኛችን ፡ ይጠብቀናል (Eregnachen Yetebeqenal) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 2.jpg


(2)

አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
(Amien Belu Segedulet)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 3:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

የጠላትን ፍላፃ ሰብሮ እኛን የከለለ ፈጥኖ
ከቅጥራችን ኋላ የቆመው የእሳት ነበልባል የሆነልን
ዘንዶውን ደርሶ ቀጠቀጠው ወጥመዱን ሰብሮ ከእግራችን በታች ጣለው

አዝ፦ እረኛችን ይጠብቀናል ከአዳኝ ወጥመድ አስጥሎናል
ወጥመድ ተሰብሮ እኛ አምልጠናል
ረድኤታችን ተዋግቶልናል (3)

ሰልፉ ደርቶ ውጊያው ጠንክሮ የጦሩ ሜዳ ደም ተነክሮ
ጠላት ሲያይል ጌታን ጠራነው በውጊያው ሜዳ ቅደም አልነው
እርሱም በበቀል ከፍ አለልን ባምላካችን ኃይል ከቅጥሩ በላይ ቆምን

አዝ፦ እረኛችን ይጠብቀናል ከአዳኝ ወጥመድ አስጥሎናል
ወጥመድ ተሰብሮ እኛ አምልጠናል
ረድኤታችን ተዋግቶልናል (3)

ሃሌሉያ ጌታ አቁሞናል የሱስ በፍቅሩ ታድጎናል
ከእርሱ ሽተን ፍርድ አላጣንም በጠላት ወጥመድ ውስጥ አልገባንም

አበቃ ያሉን አለቀላቸው በበረታች ክንድ በእሳቱ በተናቸው