ብርቱ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (Bertu New Egziabhier) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 2.jpg


(2)

አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
(Amien Belu Segedulet)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አዝ፦ ብርቱ ነው እግዚአብሔር ብርቱ ነው ብርቱ ነው እርሱ ብርቱ ነው
የፈርኦንን ሠራዊት ያሰጠመው ብርቱ ነው እኛም አየነው

ጭንቀት ከቦን ሳለ በዙሪያችን መንምኖ ጠፍቶብን እምነታችን
አትጣለን ብለን ተማፀንን የእስራኤል ታዳጊ ደረሰልን
አንደበት ማዳኑን ይንገርልን

አዝ፦ ብርቱ ነው እግዚአብሔር ብርቱ ነው ብርቱ ነው እርሱ ብርቱ ነው
የፈርኦንን ሠራዊት ያሰጠመው ብርቱ ነው እኛም አየነው

ሰይጣን እንደስንዴ ሊያበጥረን ባለው ጉልበት ኃይሉ ተነሳብን
ግን ጌታ ኢየሱስ ማለደልን ይኸው ዛሬ ፊቱ በድል ቆምን
ሌላማ ምን አለን ይክበርልን

አዝ፦ ብርቱ ነው እግዚአብሔር ብርቱ ነው ብርቱ ነው እርሱ ብርቱ ነው
የፈርኦንን ሠራዊት ያሰጠመው ብርቱ ነው እኛም አየነው

ተስፋ ያጣንበት ነገራችን ዛሬ ታደሰልን በጌታችን
ፊቱ እንቆማለን በምስጋና አልአዛር ዳግም ሰው ሆኗልና
ለጌታ የሚሳነው የለምና

አዝ፦ ብርቱ ነው እግዚአብሔር ብርቱ ነው ብርቱ ነው እርሱ ብርቱ ነው
የፈርኦንን ሠራዊት ያሰጠመው ብርቱ ነው እኛም አየነው

ኤልዛቤል በቁጣ ስትናገ ልባችን በፍርሃት ቀልጦ ነበር
በማይታጠፈው ክንዱ ጌታ ደግፎ አቆመን እንዳንረታ
ብርቱ ነው እንላለን ጠዋት ማታ

አዝ፦ ብርቱ ነው እግዚአብሔር ብርቱ ነው ብርቱ ነው እርሱ ብርቱ ነው
የፈርኦንን ሠራዊት ያሰጠመው ብርቱ ነው እኛም አየነው