በደስታ ፡ ሃሌሉያ (Bedesta Haleluya) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 2.jpg


(2)

አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
(Amien Belu Segedulet)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 3:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አዝ፦ በደስታ ሃሌሉያ በእልልታ አሜን (፪x)
ጌታ መገለጡን እንጠብቃለን

ጌታችን ሊገለጥ ተዳርሷል ሰዓቱ
የተሰጠን ተስፋ ሊሞላ ትንቢቱ
ሊታመን በቃሉ ጥቂት አይዘገይም
ፍጥረታት ቢጠፉ ቃሉ ግን አያልፍም

አዝ፦ በደስታ ሃሌሉያ በእልልታ አሜን (፪x)
ጌታ መገለጡን እንጠብቃለን

ፀሐይቱ ስትጨልም ጨረቃዋም አብራ
ከዋክብት ሊጠፉ ሊመጣ መከራ
የምድር ሃያላት ሁሉ ሊናወጡ
ጭንቀትም ሊበዘ ድንጋጤ ምጡ

አዝ፦ በደስታ ሃሌሉያ በእልልታ አሜን (፪x)
ጌታ መገለጡን እንጠብቃለን

የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ሊሉ
ኢየሱስን ከላይ ከሰማይ ያያሉ
ጌታችን ሲገለጥ በክብር በግርማ
እኛ አንሸበርም የመጣው ለኛ ነው

አዝ፦ በደስታ ሃሌሉያ በእልልታ አሜን (፪x)
ጌታ መገለጡን እንጠብቃለን

ሊወስደን ከቦታው ካበጀልን ሥፍራ
ባባቱ ዙፋን ሥር በፅዮን ተራራ
ከምድር መከራ ሊሰጠንም እረፍት
መሄዳችን አይቀር ቢመስልም ሞኝነት