አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት (Amien Belu Segedulet) - አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 2.jpg


(2)

አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
(Amien Belu Segedulet)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 3:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስ ፡ አበባ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

1. ባህር ተናወጠች ተራሮችም ጨሱ
  የሰማያት አምላክ ወጣ ከመቅደሱ
  ክብሩ ምድርን ሞላ ቁጣውም ነደደ
  ለልጆቹ ሊያግዝ ጌታችን ወረደ

አዝ፦ አሜን በሉ ስገዱለት
ለዚህ አምላክ እኛን ለረዳን
ውርደትን በክብር ለውጦ
ጠላታችንንም ቀጥቅጦ እኛን ላበዛ
አሜን በሉ ስገዱለት

2.እግዚአብሔር ነገሠ አህዛብ ደነገጡ
  በኪሩቤል ዙፋን ላይ በመቀመጡ
  እነዚያ በፈረስ በሰረገላቸው
  ቢታመኑበትም ጌታ አሳፈራቸው

አዝ፦ አሜን በሉ ስገዱለት
ለዚህ አምላክ እኛን ለረዳን
ውርደትን በክብር ለውጦ
ጠላታችንንም ቀጥቅጦ እኛን ላበዛ
አሜን በሉ ስገዱለት

3.ድምፁ እንደነጎድጓድ ክብርን የለበሰ
  የፊቱ ብርሃን ከፀሐይ የባሰ
  ፈነጠቀባቸው የብርሃኑን ጮራ
  እንዳለ ሊያስታውቅ ከልጆቹ ጋራ

አዝ፦ አሜን በሉ ስገዱለት
ለዚህ አምላክ እኛን ለረዳን
ውርደትን በክብር ለውጦ
ጠላታችንንም ቀጥቅጦ እኛን ላበዛ
አሜን በሉ ስገዱለት

4.ምድርና ሞላዋ የአምላካችን ናት
  ዓለምና በእርሷ ሁሉ የሚኖሩት
  እግዚአብሔር ወረደ በተራሮች መሃል
  በክብር ተሞልቶ እኛን ለመከለል