From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ የጽዮን ፡ ግርማዋ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው
በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ በላይ ፡ ያለው
የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ደግሞም ፡ የሚባለው
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ጌታችን ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው
ምድር ፡ መረገጫው ፡ ሰማይም ፡ ዙፋኑ
የጽዮን ፡ ሙሽራ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ብርሃኑ
ወጀብ ፡ ነጐድጓድም ፡ ለርሱ ፡ ይታዘዛል
ስሙ ፡ ግሩም ፡ መንፈስ ፡ ነው ፡ ሰላምን ፡ ይሰጣል
አዝ፦ የጽዮን ፡ ግርማዋ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው
በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ በላይ ፡ ያለው
የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ደግሞም ፡ የሚባለው
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ጌታችን ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ደግሞም ፡ እሩህሩህ ፡ ነው
ከአንበሳ ፡ መንጋጋ ፡ ከእሳት ፡ ያወጣ ፡ ነው
ልጆቹን ፡ ይወዳል ፡ እህል ፡ ይሰጣቸዋል
ቃሉም ፡ ለዘለዓለም ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ይኖራል
አዝ፦ የጽዮን ፡ ግርማዋ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው
በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ በላይ ፡ ያለው
የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ደግሞም ፡ የሚባለው
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ጌታችን ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነው ፡ ዘመን ፡ አይሽረውም
ሰማይ ፡ ምድር ፡ ሲያልፉ ፡ እርሱ ፡ አይለወጥም
ስሙም ፡ ለዘለዓለም ፡ ታምርን ፡ ይሰራል
ደሙ ፡ ፍጹም ፡ ኃይል ፡ ነው ፡ ሕይወትን ፡ ይሰጣል
አዝ፦ የጽዮን ፡ ግርማዋ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው
በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ በላይ ፡ ያለው
የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ደግሞም ፡ የሚባለው
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ጌታችን ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው
|