From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ስለዚህ ፡ እላችኋለሁ ፡ ስለ ፡ ነፍሳችሁ ፡ በምትበሉትና ፡
በምትጠጡት ፡ ወይም ፡ ስለ ፡ ሰውነታችሁ ፡ በምትለብሱት ፡
አትጨነቁ ። ነፍስ ፡ ከመብል ፡ ሰውነትም ፡ ከልብስ ፡ አይበልጥምን?
ወደ ፡ ሰማይ ፡ ወፎች ፡ ተመልከቱ ። አይዘሩም ፡ አያጭዱም ፡
በጐተራም ፡ አይከቱም ። የሰማዩ ፡ አባታችሁ ፡ ይመግባቸዋል ።
እናንተም ፡ ከእነርሱም ፡ እጅግ ፡ አትበልጡምን? ከእናንተ ፡ ተጨንቆ ፡
ከቁመቱ ፡ ላይ ፡ አንድ ፡ ክንድ ፡ መጨመር ፡ የሚችል ፡ ማነው?
ስለልብስስ ፡ ስለምን ፡ ትጨነቃላቹህ? የሜዳ ፡ አበቦች ፡ እንዴት ፡
እንዲያድጉ ፡ ልብ ፡ አድርጋችሁ ፡ ተመልከቱ ። አይደክሙም ፤
አይፈትሉምም ። ነገር ፡ ግን ፡ እላችኋለሁ ፡ ሰለሞንስ ፡ እንኳን ፡
በክብሩ ፡ ሁሉ ፡ ከነዚህ ፡ እንደ ፡ አንዱ ፡ አልለበሰም ።
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ዛሬ ፡ ያለውን ፡ ነገም ፡ ወደ ፡ እቶን ፡ የሚጣለውን ፡
የሜዳን ፡ ሳር ፡ እንዲህ ፡ የሚያለብሰው ፡ ከሆነ ፣ እናንተ ፡ እምነት ፡
የጐደላችሁ ፡ እናንተንማ ፡ ይልቁን ፡ "እንዴት ፡ እንግዲህ ፡
ምን ፡ እንበላለን? ምንስ ፡ እንጠጣለን? ምንስ ፡ እንለብሳለን?" ብላችሁ ፡
አትጨነቁ ። ይህንስ ፡ ሁሉ ፡ አሕዛብ ፡ ይፈልጋሉ ። ይህ ፡ ሁሉ ፡
እንዲያስፈልጋችሁ ፡ የሰማዩ ፡ አባታችሁ ፡ ያውቃልና ። ነገር ፡ ግን ፡
አስቀድማችሁ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ መንግስት ፣ ጽድቁንም ፡ ፈልጉ ።
ይህም ፡ ሁሉ ፡ ይጨመርላችኋል ። ነገ ፡ ለራሱ ፡ ይጨነቃልና ፡
ለነገ ፡ አትጨነቁ ። ለቀኑ ፡ ክፋቱ ፡ ይበቃዋል ። ነገ ፡ ለራሱ ፡
ይጨነቃልና ፡ ለነገ ፡ አትጨነቁ ። [1]
አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ
የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
ነገ ፡ ለሚሆነው ፡ ብጨነቅ ፡ ባዝን
ትርፉ ፡ ማጉረምረም ፡ ነው ፡ ጌታንም ፡ ማሳዘን
ጨንቀቴን ፡ ሁሉ ፡ ለጌታ ፡ ማስረከብ ፡ ነው
ስለእኔ ያስባል ፡ እርሱ ፡ አባቴ ፡ ነው
የእኔ ፡ ነገ ፡ ሙሉ ፡ ፀሐይ ፡ ነው
የሚያዝበትም ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ
የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
የነገ ፡ ውለቴ ፡ በጌታ ፡ እጅ ፡ ነው
ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ በእርሱ ፡ ቁጥጥር ፡ ነው
የሰማዩ ፡ አባቴ ፡ በነገው ፡ አልፎበታል
ደመናው ፡ ይጠፋል ፡ ሃዘን ፡ ደስታ ፡ ይሆናል
የእኔ ፡ ነገ ፡ ተስፋ ፡ ያለው ፡ ነው
ተቆጣጣሪው ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ
የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
ፈተናም ፡ ችግር ፡ መከራም ፡ ቢሆን
ያለአባቴ ፡ ፈቃድ ፡ አንዳችም ፡ ላይሆን
ፈቃዱም ፡ ከሆነ ፡ ክፉ ፡ ለበጐ ፡ ነው
የኔም ፡ ነገ ፡ ሁልጊዜም ፡ ብርሃን ፡ ነው
የእኔ ፡ ነገ ፡ ብሩህ ፡ ፀሐይ ፡ ነው
የሚያዝበትም ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ
የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
ሞት ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ ለእኔ ፡ ጥቅም ፡ ነው
ከጌታ ፡ ጋር ፡ መሆን ፡ እጅግ ፡ የሚሻል ፡ ነው
ጨለማ ፡ ይጠብቀኝ ፡ ተስፋዬ ፡ ብሩህ ፡ ነው
የፍጻሜው ፡ እድሌ ፡ የኔስ ፡ ትንሳኤ ፡ ነው
የእኔ ፡ ነገ ፡ ፍፁም ፡ ብርሃን ፡ ነው
ይሁን ፡ ያለውም ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
አዝ፦ የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ
የእኔ ፡ ነገ ፡ ለኔስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
|
- ↑ ማቴዎስ ፮ ፡ ፳፭ - ፴፬ (Matthew 6:25-34)