ሰው ፡ ሆይ ፡ ክብርን (Sew Hoy Kebren) - መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ
(Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold 2.jpg


(2)

ዝናህ ፡ የገነነው
(Zenah Yegenenew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ ፡ አልበሞች
(Albums by Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

ሰው ፡ ሁሉ ፡ ነፍሱን ፡ ቢያተርፍ ፡ ለሥጋው
መዝገቡ ፡ ቢሆን ፡ እዚህ ፡ ምድራዊ
ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምንስ ፡ ሊጠቅመው
ሕይወትን ፡ ትቶ ፡ መሆኑ ፡ ጠፊ ፡ ሰው

አዝ፦ ሰው ፡ ሆይ ፡ ክብርን ፡ ሰው ፡ ሆይ ፡ አትይ
ዕውቀት ፡ ጥበብን ፡ የዓለምን ፡ ዝና
እንቅፋት ፡ ሆኖ ፡ ጋሬጣ ፡ ሆኖ
ከአምላክህ ፡ እንዳይለይህ (፪x)

የእግዚአብሔር ፡ አምሳል ፡ ክብር ፡ ያለበት
ሰው ፡ ውድ ፡ ነበረ ፡ እርሱ ፡ ቢያውቅበት
በገነት ፡ ምድር ፡ ሊኖር ፡ በደስታ
ነበር ፡ አላማው ፡ ሲፈጥረውማ ፡ ጌታ

አዝ፦ ሰው ፡ ሆይ ፡ ክብርን ፡ ሰው ፡ ሆይ ፡ አትይ
ዕውቀት ፡ ጥበብን ፡ የዓለም ፡ ዝና
እንቅፋት ፡ ሆኖ ፡ ጋሬጣ ፡ ሆኖ
ከአምላክህ ፡ እንዳይለይህ (፪x)

ብናኝ ፡ አቧራ ፡ ውዳቂ ፡ ጠፊ
ነው ፡ የሰው ፡ ትምክቱ ፡ ደግሞም ፡ አላፊ
ሰው ፡ ሆይ ፡ ከአምላክህ ፡ ብትስማማ
በርሱ ፡ እጅ ፡ ነበር ፡ ብሩና ፡ ወርቁማ

አዝ፦ ሰው ፡ ሆይ ፡ ክብርን ፡ ሰው ፡ ሆይ ፡ አትይ
ዕውቀት ፡ ጥበብን ፡ የዓለም ፡ ዝና
እንቅፋት ፡ ሆኖ ፡ ጋሬጣ ፡ ሆኖ
ከአምላክህ ፡ እንዳይለይህ (፪x)