ኦሆሆ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ (Ohoho Bemeder Lay Ohoho Besemay) - መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ
(Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold 2.jpg


(2)

ዝናህ ፡ የገነነው
(Zenah Yegenenew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ ፡ አልበሞች
(Albums by Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

አዝ፦ ኦሆሆ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ
እልልታ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እልልታ ፡ በሰማይ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ከበረ ፡ በዓለም ፡ ላይ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገሠ ፡ በዓለም ፡ ላይ (፪x)

የወንጌሉ ፡ ስራ ፡ ድንቅን ፡ አደረገ
ጸድቅን ፡ እየዘራ ፡ ፍርድን ፡ አስወገደ
ሽባው ፡ ተተርትሮ ፡ እውሩ ፡ ዐይኑ ፡ በራ
ምስኪኑ ፡ ከወድቀት ፡ ተነስቶ ፡ እግሩ ፡ ጸና

አዝ፦ ኦሆሆ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ
እልልታ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እልልታ ፡ በሰማይ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ከበረ ፡ በዓለም ፡ ላይ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገሠ ፡ በዓለም ፡ ላይ (፪x)

ለነገድ ፡ ለቋንቋ ፡ ተነገረ ፡ አዋጁ
ፍቅርን ፡ እንደሰጠን ፡ እግዚአብሔር ፡ በልጁ
የምስራቹ ፡ ቃል ፡ ሆነልን ፡ ብርሃን
በጨለማ ፡ ያሉ ፡ አዩት ፡ ጌታችንን

አዝ፦ ኦሆሆ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ
እልልታ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እልልታ ፡ በሰማይ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ከበረ ፡ በዓለም ፡ ላይ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገሠ ፡ በዓለም ፡ ላይ (፪x)

ቃሉ ፡ እየነጐደ ፡ ምድርን ፡ አለበሰ
የዲያቢሎስን ፡ ክንድ ፡ እያፈራረሰ
ለኃጢአት ፡ እስረኞች ፡ ክብደት ፡ ጸናባቸው
ኢየሱስ ፡ ዋስ ፡ ሆነና ፡ ነፃ ፡ ለቀቃቸው

አዝ፦ ኦሆሆ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ
እልልታ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እልልታ ፡ በሰማይ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ከበረ ፡ በዓለም ፡ ላይ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገሠ ፡ በዓለም ፡ ላይ (፪x)