ምድርና ፡ ሞላዋ (Mederna Molawa) - መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ
(Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold 2.jpg


(2)

ዝናህ ፡ የገነነው
(Zenah Yegenenew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ ፡ አልበሞች
(Albums by Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

እግዚአብሔር ፡ እሩህሩህና ፡ መሃሪ ፡ ነው
ከቁጣ ፡ የራቀ ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ለሚታገሱት ፡ ሁሉ ፡ ቸር ፡ ነው
ምህረቱም ፡ በስራው ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ነው

አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው
ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው
ለርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ (፪x)

ስለ ፡ ነገሠ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ስላለ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል
ግርማው ፡ ስለሚያስፈራ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል
ሥሙ ፡ ታላቅ ፡ ስለሆነ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል

አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው
ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው
ለርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ (፪x)

ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይንበረከካሉ
አፍም ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ፡ ያቀርባሉ
መላእክት ፡ በሰማይ ፡ ለክብሩ ፡ ያዜማሉ
ቅዱሳን ፡ በናፍቆት ፡ በምድር ፡ ይቀኛሉ

አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው
ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው
ለርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ (፫x)