ጉባኤውን ፡ ሁሉ ፡ ባርከው (Gubaewen Hulu Barkew) - መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ
(Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold 2.jpg


(2)

ዝናህ ፡ የገነነው
(Zenah Yegenenew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ ፡ አልበሞች
(Albums by Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

ጉባኤውን ፡ ሁሉ ፡ ባርከው ፡ ጌታ
ቃልህን ፡ ላክ ፡ ፈውስ ፡ ይሁንልን
በታላቅ ፡ መጐብኘትህ ፡ አስበን
የኋለኛውን ፡ ዝናብህን ፡ ላክልን

እሳት ፡ እሳት ፡ ያንን ፡ የመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እሳት (፪x)

ጉባኤውን ፡ ተመልከተው ፡ ጌታ
የደከመውን ፡ ሁሉ ፡ አንሳ
የላሉትንም ፡ ጉልበቶቼን ፡ ሁሉ
ለአምላካቸው ፡ ሁሉ ፡ አበርታ

ልጆቼ ፡ አይዟችሁ ፡ በለን ፡ ጌታ (፪x)

የታመሙትንም ፡ ሁሉ ፡ ፈውስ
በታላቅ ፡ ምህረትህ ፡ አስበን
የታሰሩትንም ፡ ሁሉ ፡ ፍታ
ጐብኘን ፡ የሠራዊት ፡ ጌታ

ተነስ ፡ ተነስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ክንድ ፡ ሆይ ፡ ተነስ (፪x)

ታላቁ ፡ ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ጌታ
ምህረትህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ማዳንህ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ
ክብርህ ፡ ይስፋ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ

ለዘለዓለም ፡ ክበር ፡ ሃሌሉያ (፪x)