በተከበበች ፡ ከተማ (Betekebebech Ketema) - መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ
(Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold 2.jpg


(2)

ዝናህ ፡ የገነነው
(Zenah Yegenenew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ ፡ አልበሞች
(Albums by Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

አዝ፦ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ የሚያስደንቀውን ፡ ምህረቱን
በእኔ ፡ ላይ ፡ የገለጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፪x)

ደመናም ፡ ውኃም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆውን ፡ የሚሞላ
በእርሱ እታመናለሁ ፡ በክንዶቹ ፡ ጥላ
ጌታን ፡ ተስፋ ፡ አድርገው ፡ የሚጠባበቁ
እንዳይጠፉ ፡ አውቃለሁ ፡ ከቶም ፡ እንዳይወድቁ

አዝ፦ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ የሚያስደንቀውን ፡ ምህረቱን
በእኔ ፡ ላይ ፡ የገለጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፪x)

ሰማያት ፡ ተናውጠው ፡ በክብሩ ፡ ይወርዳል
የልጆቹ ፡ ነገር ፡ ጌታ ፡ ግድ ፡ ይለዋል
ታምኜ ፡ እቆማለሁ ፡ በዓለቱ ፡ ላይ
በፍጽሜው ፡ ዘመን ፡ ዐይኖቹን ፡ እስካይ

አዝ፦ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ የሚያስደንቀውን ፡ ምህረቱን
በእኔ ፡ ላይ ፡ የገለጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፪x)

የልጅነት ፡ ስልጣን ፡ እንዲያው ፡ ተሰጥቶኛል
ስሙ ፡ በግንባሬ ፡ ማኅተም ፡ ሆኖኛል
አምላክሽ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ አትበለኝ ፡ ጠላቴ
አይቆይም ፡ ይመጣል ፡ ፈጥኖ ፡ ረዳቴ

አዝ፦ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ የሚያስደንቀውን ፡ ምህረቱን
በእኔ ፡ ላይ ፡ የገለጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፪x)