ባርነትን ፡ ሸሽተው ፡ የወጡት (Bareneten Sheshtew Yewetut) - መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ
(Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold 2.jpg


(2)

ዝናህ ፡ የገነነው
(Zenah Yegenenew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ ፡ አልበሞች
(Albums by Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

የባርነት ፡ ኑሮ ፡ ሰልችቷቸው ፡ ተመረዉ
ቅድስቲቷን ፡ ከተማ ፡ ተመኝተው ፡ ፈልገዋት
ተጨንቀህ ፡ ተጠበህ ፡ ያወጣሃቸው ፡ ምርጥህ ፡ ሕዝቦች
የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ጌታዬ ፡ ደምህ ፡ ፍሬዎች

አዝ፦ ባርነትን ፡ ሸሽተው ፡ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ የወጡት
የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ከነአንን ፡ ሳያይዋት
ጌታ ፡ መልሳቸው ፡ ወደ ፡ መንጐችህ ፡ በረት
በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ሳይደርስባቸው ፡ የፍርድ ፡ እለት

ሲያለቅሱ ፡ በምኞት ፡ እጅግ ፡ ናፍቀው ፡ ያቺን ፡ ሃገር
ደግሞም ፡ እየጠጡ ፡ የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ በፍቅር
ጸጋር ፡ በዝቶላቸው ፡ የነበሩት ፡ በአገልግሎት
ምን ፡ ጠቃሚ ፡ አገኙና ፡ ጥለውህ ፡ ሄዱ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ

አዝ፦ ባርነትን ፡ ሸሽተው ፡ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ የወጡት
የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ከነአንን ፡ ሳያይዋት
ጌታ ፡ መልሳቸው ፡ ወደ ፡ መንጐችህ ፡ በረት
በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ሳይደርስባቸው ፡ የፍርድ ፡ እለት

በምህረትህ ፡ አቅፈህ ፡ አሳድገህ ፡ በአንተ ጉያ
እንዴት ፡ ይችሉታል ፡ የበረሃውን ፡ መሰማሪያ
የሕይወቱን ፡ ውኃ ፡ እየጠጡ ፡ ያደጉትን
እንዴት ፡ ይችሉታል ፡ የበረሃውን ፡ ጥማትን

አዝ፦ ባርነትን ፡ ሸሽተው ፡ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ የወጡት
የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ከነአንን ፡ ሳያይዋት
ጌታ ፡ መልሳቸው ፡ ወደ ፡ መንጐችህ ፡ በረት
በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ሳይደርስባቸው ፡ የፍርድ ፡ እለት

የደምህን ፡ ፍሬ ፡ ዘርተህ ፡ ነበር ፡ በጭንቅ ፡ ጌታ
አድገዋል ፡ ሲባሉ ፡ ጠወለጉና ፡ ጠፉ ፡ ጌታ
ኧረ ፡ መልሳቸው ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለደምህ
ወደ ፡ ለምለም ፡ ይምጡ ፡ ከበረሃው ፡ ግልገሎችህ

አዝ፦ ባርነትን ፡ ሸሽተው ፡ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ የወጡት
የት ፡ ሄደው ፡ አለቁ ፡ ከነአንን ፡ ሳያይዋት
ጌታ ፡ መልሳቸው ፡ ወደ ፡ መንጐችህ ፡ በረት
በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ሳይደርስባቸው ፡ የፍርድ ፡ እለት