እግዚአብሔር ፡ አለ (Egziabhier Ale) - መሠረት ፡ ፅጌ ፡ እና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረት ፡ ፅጌ ፡ እና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ
(Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold 1.jpg


(1)

የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ
(Yeadis Kidan Beg)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 3:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረት ፡ ፅጌ ፡ እና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ ፡ አልበሞች
(Albums by Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ በላይ ፡ በክብሩ
ይገዙለታል ፡ ለእርሱ ፡ ሰማይና ፡ ምድሩ
ለማያምኑት ፡ ሞኝነት ፡ ነው
ለእኛ ፡ ግን ፡ ሕይወት ፡ ነው ፡ ሃሌሉያ (፪x)

እናውጃለን ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
እንመሰክራለን ፡ እኛ ፡ ፈጣሪ ፡ አለ
ለምንድነው ፡ ተስፋችን ፡ ነው
ለማያምኑት ፡ ግን ፡ ጥፋት ፡ ነው
(፪x)

ለውጦናል ፡ እኛን ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
በቃሉ ፡ አናምናለን ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
ለምንድነው ፡ ሕይወታችን ፡ ነው
ለሚጠፉት ፡ ግን ፡ ሞት ፡ ነው (፪x)

ሲሰራ ፡ አይተናል ፡ እና ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
ፍቅሩንም ፡ ቀምሰናል ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
ፈውስን ፡ በልጁ ፡ አግኝተናል
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ሰጥቶናል
(፪x)

ክብሩን ፡ አይተናል ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
እንመሰክራለን ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
መስቀሉን ፡ ለእኛ ፡ ክብራችን ፡ ነው
ሕይወት ፡ ሰላማችን ፡ ሃይላችን ፡ ነው (፪x)