ወዶኛል (Wedognal) - መንግሥቱ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መንግሥቱ ፡ ከበደ
(Mengistu Kebede)

Mengistu Kebede 1.jpg


(1)

ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ
(Zarem Gulbetam Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 3:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመንግሥቱ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Mengistu Kebede)

ዙፋኑን ፡ ትቶ ፡ ወረደ
ፈልጐ ፡ እኔን ፡ ሊያገኘኝ
ሳልወደው ፡ ቀድሞ ፡ ወደደኝ
ከዓለም ፡ ለይቶ ፡ መረጠኝ
በውርደት ፡ ሞትን ፡ ከመሞት
ፍቅሩን ፡ ለእኔ ፡ ገለጠልኝ
ከዘለዓለም ፡ ፍቅር ፡ ስቦ
ወደ ፡ እልፍኙ ፡ አስገባኝ

አዝውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ ለዘላዓለም ፡ ነው
ወዶኛል ፡ ወድጄዋለሁ
እንደርሱ ፡ የታለ ፡ ማነው (፪x)

ማንም ፡ መጥቶ ፡ አይነጥለኝ
አንዴ ፡ የእራሱ ፡ አድርጐኛል
ይተወኛል ፡ ብዬ ፡ አልፈራም
የከሳሼን ፡ ወሬ ፡ አልሰማም
ወረተኛ ፡ አይደል ፡ እንደሰው ፡ ለዘለዓለም ፡ ወዶኛል
ጥፋት ፡ እንኳን ፡ ሲያገኝብኝ ፡ በፍቅር ፡ መክሮ ፡ ያድነኛል

አዝውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ ለዘላዓለም ፡ ነው
ወዶኛል ፡ ወድጄዋለሁ
እንደርሱ ፡ የታለ ፡ ማነው (፪x)

ግርማው ፡ በቃል ፡ አይገለጽ
ፊቱ ፡ እንደፀሐይ ፡ ሲያበራ
ከእኔ ፡ ወዳጅ ፡ አይበልጥም
ማንም ፡ በምንም ፡ ቢጠራ
በእርሱ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ሁልጊዜ ፡ ሃሴት ፡ አደርጋለሁ
ኩራት ፡ ኩራት ፡ ይሰማኛል
የእርሱ ፡ መሆኔ ፡ አርክቶኛል

አዝውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ ለዘላዓለም ፡ ነው
ወዶኛል ፡ ወድጄዋለሁ
እንደርሱ ፡ የታለ ፡ ማነው (፪x)

ይታወቅ ፡ በምድር ፡ ሁሉ
እኔ ፡ ኢየሱስን ፡ መውደዴ
ያኮራል ፡ ያስመካል ፡ እንጂ
አያሳፍረኝም ፡ ውዴ
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ የምሆንበት
የሠርጌን ፡ ቀን ፡ ናፍቄያለሁ
ነፍሴን ፡ በደሙ ፡ አንጽቼ
ምጻቱን ፡ እጠብቃለሁ

አዝውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ ለዘላዓለም ፡ ነው
ወዶኛል ፡ ወድጄዋለሁ
እንደርሱ ፡ የታለ ፡ ማነው (፪x)