መላኩ ማርቆስ (Melaku Markos)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, searchብዬዋለሁ የኔ ጌታ ስለሆነልኝ መከታ ታሪክ ሰርቶ በህይወቴ አስደነቀኝ መድሀኒቴ

ምንም ሳይቸግረው ለኔ ሲል ተጎዳ ሲመቱት ሲገርፉት አርገው እንደ ባዳ የእየሱሴ ቁስል ለእኔ ፈውስ ሆኖልኝ ነፃ አውጥቶኛል ከፍ ይበልልኝ

ብዬዋለሁ የኔ ጌታ ስለሆነልኝ መከታ
 ታሪክ ሰርቶ በህይወቴ አስደነቀኝ መድሀኒቴ 

ከሞት አመለጥኩኝ በርሱ ተደግፌ(2) በህይወት አለሁኝ ከስቃይ አርፌ (2) ከዚያ ከጨለማ አወጣኝ መንጥቆ (2) ወዶ አከበረኝ ለኔ ሲል ተንቆ(2።

የማይከዳ የቅርብ ኋደኛ የሚራራ ወዳጅ ነው እርሱ
ጠርቶ መንገድ ላይ ጥሎ ለማይሸሽ ለሚጎበኘን በመንፈሱ
   ክብር ይሁን ለንጉሡ4×

እዳዬን ሊከፍል መስቀል ተሸክሞ ምራቅ እየተፉ ሲስቁበት ቆሞው በኔ ፈንታ ሞቶ ህይወቱን ሰጠኝ በዘላለም ፍቅሩ እኔን ወደደኝ

የማይከዳ የቅርብ ኋደኛ የሚራራ ወዳጅ ነው እርሱ
ጠርቶ መንገድ ላይ ጥሎ ለማይሸሽ ለሚጎበኘን በመንፈሱ
   ክብር ይሁን ለንጉሡ4×