የምስራቹ ፡ ቃል (Yemeserachu Qal) - መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት
(Mekrez Youth Ministry)

Lyrics.jpg


(3)

የምስራቹ ፡ ቃል
(Yemeserachu Qal)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Mekrez Youth Ministry)

ጌታህን ፡ አመስግን ፡ ክርስቲያን ፡ ተነሳ
ልብህን ፡ ከእጆችህ ፡ ጋር ፡ ወደ ፡ አምላክህ ፡ አንሳ
ኢየሱስ ፡ ተወልዷል ፡ ምስራች ፡ ተናገር
እግዚአብሔር ፡ አምላክህን ፡ አመስግን ፡ በመዝሙር

አዝ፦ የምስራቹ ፡ ቃል ፡ በምድር ፡ ተሰማ
በከብቶች ፡ በረት ፡ ውስጥ ፡ ቤትለሄም ፡ ከተማ
ምንም ፡ ጊዜው ፡ ቢረዝም ፡ ቢታይም ፡ እርቆ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ ዘመኑን ፡ ጠብቆ

የአዋጅ ፡ ነጋሪ ፡ ድምጽ ፡ በምድር ፡ ሲያስተጋባ
የነብያት ፡ ትንቢት ፡ ፍፁም ፡ ሳይዛባ
ኢየሱስ ፡ ተወልዷል ፡ ለሰው ፡ መዳን ፡ ሆኗል
ዕልል ፡ በል ፡ ተናገር ፡ የምስራቹን ፡ ቃል

አዝ፦ የምስራቹ ፡ ቃል ፡ በምድር ፡ ተሰማ
በከብቶች ፡ በረት ፡ ውስጥ ፡ ቤትለሄም ፡ ከተማ
ምንም ፡ ጊዜው ፡ ቢረዝም ፡ ቢታይም ፡ እርቆ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ ዘመኑን ፡ ጠብቆ

የቀደመው ፡ አዳም ፡ ቢሞት ፡ በሃጥያቱ
አምላክ ፡ አልተወንም ፡ አልቆበት ፡ ምህረቱ
አማኑኤል ፡ ተወልዷል ፡ ምድር ፡ ታስተጋባ
አመስግን ፡ በአፍህ ፡ በእጆችህ ፡ ጭብጨባ

አዝ፦ የምስራቹ ፡ ቃል ፡ በምድር ፡ ተሰማ
በከብቶች ፡ በረት ፡ ውስጥ ፡ ቤትለሄም ፡ ከተማ
ምንም ፡ ጊዜው ፡ ቢረዝም ፡ ቢታይም ፡ እርቆ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ ዘመኑን ፡ ጠብቆ (፪x)

አዝ፦ የምስራቹ ፡ ቃል ፡ በምድር ፡ ተሰማ
በከብቶች ፡ በረት ፡ ውስጥ ፡ ቤትለሄም ፡ ከተማ
ምንም ፡ ጊዜው ፡ ቢረዝም ፡ ቢታይም ፡ እርቆ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ ዘመኑን ፡ ጠብቆ (፪x)