ጥቅስ ፡ በእምነት (Teqs Bemnet) - መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት
(Mekrez Youth Ministry)

Lyrics.jpg


(3)

የምስራቹ ፡ ቃል
(Yemeserachu Qal)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 1:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Mekrez Youth Ministry)

በዚያም ፡ ምድር ፡ መንጋቸውን ፡ በሌሊት ፡ ሲጠብቁ ፡ በሜዳ ፡ ያደሩ ፡ እረኞች ፡ ነበሩ።
እነሆም ፥ የጌታ ፡ መልአክ ፡ ወደ ፡ እነርሱ ፡ ቀረበ ፡ የጌታ ፡ ክብርም ፡ በዙሪያቸው ፡ አበራ ፥
ታላቅ ፡ ፍርሃትም ፡ ፈሩ። መልአኩም ፡ እንዲህ ፡ አላቸው።
እነሆ ፥ ለሕዝቡ ፡ ሁሉ ፡ የሚሆን ፡ ታላቅ ፡ ደስታ ፡ የምሥራች ፡ እነግራችኋለሁና ፡ አትፍሩ ፤
ዛሬ ፡ በዳዊት ፡ ከተማ ፡ መድኃኒት ፡ እርሱም ፡ ክርስቶስ ፡ ጌታ ፡ የሆነ ፡ ተወልዶላችኋልና።
ይህም ፡ ምልክት ፡ ይሆንላችኋል ፤ ሕፃን ፡ ተጠቅልሎ ፡ በግርግምም ፡ ተኝቶ ፡ ታገኛላችሁ።
ድንገትም ፡ ብዙ ፡ የሰማይ ፡ ሠራዊት ፡ ከመልአኩ ፡ ጋር ፡ ነበሩ። እግዚአብሔርንም ፡ እያመሰገኑ።
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ በአርያም ፡ ይሁን ፡ ሰላምም ፡ በምድር ፡ ለሰውም ፡ በጎ ፡ ፈቃድ።
መላእክትም ፡ ከእነርሱ ፡ ተለይተው ፡ ወደ ፡ ሰማይ ፡ በወጡ ፡ ጊዜ ፥ እረኞቹ ፡ እርስ ፡ በርሳቸው።
እንግዲህ ፡ እስከ ፡ ቤተ-ልሔም ፡ ድረስ ፡ እንሂድ
እግዚአብሔርም ፡ የገለጠልንን ፡ ይህን ፡ የሆነውን ፡ ነገር ፡ እንይ ፡ ተባባሉ።
ፈጥነውም ፡ መጡ ፡ ማርያምንና ፡ ዮሴፍን ፡ ሕፃኑንም ፡ በግርግም ፡ ተኝቶ ፡ አገኙ። [1]

  1. ሉቃስ ፪: ፰-፲፭ (Luke 2:8-15)