ኦ ፡ ቅዱስ ፡ ሌት (O Qedus Liet) - መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት
(Mekrez Youth Ministry)


(3)

የምስራቹ ፡ ቃል
(Yemeserachu Qal)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Mekrez Youth Ministry)

ኦ ፡ ቅዱስ ፡ ሌት ፡ ከዋክብት ፡ ያበራሉ
የአዳኛችን ፡ ልደት ፡ ስለሆነ
ዓለም ፡ በኃጢአት ፡ ውስት ፡ ስትጨማለቅ
መጣላት ፡ ተስፋዋን ፡ ስትጠብቅ
ግሩም ፡ ተስፋ ፡ ነፍሳቸውን ፡ ያረካል
ደስ ፡ ይበለን ፡ ንጋት ፡ ሆኖልናል
ስገዱለት ፡ የመላዕክቱን ፡ ድምጽ ፡ ስሙ
በቅዱሴ ፡ በክርስቶስ ፡ ልደት
ቅዱስ ፡ መዝሙር ፡ ለእርሱ ፡ አቅርቡለት

ኢየሱስ ፡ የተወለደበት ፡ ያ ፡ ዕለት
ከዋክብት ፡ በድምቀት ፡ ያበሩበት
ሃሌሉያ

በእምነት ፡ ኃይል ፡ በብርሃኑ ፡ ተመርተን
በደስታ ፡ ልብ ፡ እንይ ፡ ያንን ፡ ህጻን
የኮከቡ ፡ ብርሃን ፡ አይተው ፡ ሲሮጡ
ጥበበኞች ፡ ከሩቅ ፡ ሃገር ፡ መጡ
ህጻኑ ፡ ንጉሥ ፡ በበረት ፡ ተኝቷል
በችግር ፡ ወንድማችን ፡ ሆኗል
የእኛን ፡ ሃሳብ ፡ ድካማችንን ፡ ሁሉ
እርሱ ፡ ያውቃል ፡ ወድቀን ፡ እንስገድለት
የእኛ ፡ ንጉሥ ፡ ተወልዷል ፡ በበረት

በዚህ ፡ በገና ፡ ሰሞን ፡ የክርስቶስን ፡ ልደት ፡ ስናከብር
የእግዚአብሔርን ፡ ፍቅር ፡ የፍቅሩን ፡ ጥልቀት ፡ እናስተውላለን
በየትናውም ፡ ቦታ ፡ የምትኖሩ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ወገኖች
ኑ ፡ ኑ ፡ ኑ ፡ አክብሩት
ሃሌሉያ